ተስፋ ሰጪው የበቆሎ ሰብል በአማራ ክልል፤

በአማራ ክልል በመጪው ታህሳስ ወር መጀመሪያ ከሚሰበሰበው የበቆሎ ምርት 15.8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል፤ በ25 ወረዳዎች፣ በ541 ቀበሌዎች፣ በ3,332 ክላስተሮች በተደራጁ 570,995 አርሶ አደሮች የለማው የበቆሎ እርሻ 263,380 ሄክታር መሬት ይሸፍናል፡፡ ይህም ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት ሰፊ የአገር ውስጥ ገበያ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡ በቆሎ በግ.ት.ኤ. የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮጀክት ድጋፍ ከሚመረቱ ሰብሎች አንዱ ሲሆን የበቆሎ አምራች … Continued

ከአማራ ክልል 1600 ኩንታል የአቮካዶ ምርት ወደ ውጪ ገበያ ተጓዘ።

ከኢትዮጵያ መነሻውን ያደረገው በአማራ ክልል በ200 ሄክታር መሬት ላይ የተመረተ 1600 ኩንታል የአቮካዶ ምርት፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ከሚሰራባቸው ወረዳዎች አንዱ ከሆነው ምዕራብ ጎጃም ዞን ፣ሰሜን ሜጫ ወረዳ ተነስቶ የውጪ ገበያውን ተቀላቅሏል። በወረዳው አቮካዶ ከሚያመርቱ 447 አርሶ አርሶአደሮች ውስጥ ልፋታቸው ፍሬ አፍርቶ ምርቱ ደርሶላቸው ወደ ውጪ የላኩት 156 አርሶአደሮች ናቸው፡፡ ከእነዚህ አርሶአደሮች ተሰብስቦና ተገቢውን ምዘና አልፎ … Continued

የኢትዮጵያን ስም የያዙ የአቮካዶ ምርቶች ለአለምዓቀፍ ገበያ፤

በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ላይ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ እየመከረና በተግባርም እያገዘ አርሶ አደሩ ያመረታቸው የአቮካዶ ምርቶች የአገርን ስም ይዘው ለገበያ ሊሸኙ እየተዘጋጁ ነው። የሶስት ዓመት ትጋት እና እንክብካቤ ፍሬ አፍርቶ ለአለም ገበያ ለማቅረብ ሲሰራ የመጨረሻውን ዝግጅት ተመለከትን። እያንዳንዱ የአቮካዶ ፍሬ መጠን በኪሎ ግራም ተለክቶ በየማሸጊያው በብዛት 24 እየተደረገ በካርቶን ማሸጊያ ይሞላል። በአቮካዶ የተሞሉት ካርቶኖች ለማጓጓዝ እንዲመች … Continued

በኦሮሚያ ክልል ሉሜ ወረዳ ለውጪ ገበያ ዝግጁ የሆነ የአቮካዶ ምርት ተሰበሰበ።

በግ.ት.ኤ. ድጋፍ አቮካዶ በማምረት እና ወደ ውጪ ለመላክ ምርት በመሰብሰብ ላይ የሚገኙት አርሶ አደር አቶ አሸናፊ አያሌው ማሳ ተገኝተን ምርት ሲሰበሰብ ተመልክተናል። አቶ አሸናፊ በ2 ሄክታር መሬት ላይ ያለሙትን የአቮካዶ ተክል ላለፉት 3 ዓመታት ሲንከባከቡ ቆይተው ዛሬ ፍሬው ደርሶ ለገበያ ለማቅረብ ሽር ጉድ እያሉ ይገኛሉ። አርሶአደሩ ያመረቱትና በውጪ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው ሃስ የአቮካዶ … Continued

ግ.ት.ኤ ከልማት አጋሮቹ ጋር በመሆን የሁለት ቀን የመስክ ጉብኝት አደረገ ።

መስከረም 18፣ 2014 በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ በኩታገጠም ፕሮግራም የተዘሩ እርሻዎች ላይ በተደረገው የሁለት ቀን የመስክ ጉብኝት ከምስራቅ ሸዋ ሉሜ ወረዳ ወደ አውሮፓ ለመላክ ዝግጅቱን ያጠናቀቀውን የአቮካዶ ምርት ተመልክተዋል ። ልዑኩ በተጨማሪም በኢተያ ወረዳ የሴቶች ክላስተርን ጎብኝቷል ይህም በኩታገጠም ፕሮግራም ተሳትፎ የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት የሚጨምር ነው ። ግትኤ አጋሮቹን በኢትዮጵያ የኔዘርላንድስ ኤምባሲ፣ የዴንማርክ ኤምባሲ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ … Continued