በግ.ት.ኤ. ድጋፍ አቮካዶ በማምረት እና ወደ ውጪ ለመላክ ምርት በመሰብሰብ ላይ የሚገኙት አርሶ አደር አቶ አሸናፊ አያሌው ማሳ ተገኝተን ምርት ሲሰበሰብ ተመልክተናል።
አቶ አሸናፊ በ2 ሄክታር መሬት ላይ ያለሙትን የአቮካዶ ተክል ላለፉት 3 ዓመታት ሲንከባከቡ ቆይተው ዛሬ ፍሬው ደርሶ ለገበያ ለማቅረብ ሽር ጉድ እያሉ ይገኛሉ። አርሶአደሩ ያመረቱትና በውጪ ገበያ ላይ ከፍተኛ ተፈላጊነት ያለው ሃስ የአቮካዶ ዝርያ ከአንድ ዛፍ በአማካኝ እስከ 50 ኪሎ ድረስ እንደሚገኝበት ይናገራሉ።
ግ.ት.ኤ. ባለፉት ሦስት ዓመታት በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ትግራይና ደቡብ ክልሎች የአቮካዶ ምርት በስፋት እንዲመረትና ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የአቮካዶ ምርት እንደሌሎች የሰብል አይነቶች ጎተራ ገብቶ ገበያ እስከሚገኝ ለመጠበቅ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም፤ ይህን ቀድሞ ያሰበው ግ.ት.ኤ. ለአርሶ አደሮቹ የገበያ ትስስር ለመፍጠር ሲሰራ ቆይቷል፤ ጎን ለጎን ሲሰሩ የነበሩ ስራዎች ፍሬ አፍርተው የአቶ አሸናፊና በተመሳሳይ ግዜ የተተከሉ የሌሎች አርሶአደሮች የአቮካዶ ምርት ለውጪ ገበያ እንዲውሉ በመሰብሰብ ላይ ይገኛሉ።
Facebook
Twitter
LinkedIn