በኦሮሚያ ክልል ሞጆ ላይ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ እየመከረና በተግባርም እያገዘ አርሶ አደሩ ያመረታቸው የአቮካዶ ምርቶች የአገርን ስም ይዘው ለገበያ ሊሸኙ እየተዘጋጁ ነው።
የሶስት ዓመት ትጋት እና እንክብካቤ ፍሬ አፍርቶ ለአለም ገበያ ለማቅረብ ሲሰራ የመጨረሻውን ዝግጅት ተመለከትን። እያንዳንዱ የአቮካዶ ፍሬ መጠን በኪሎ ግራም ተለክቶ በየማሸጊያው በብዛት 24 እየተደረገ በካርቶን ማሸጊያ ይሞላል። በአቮካዶ የተሞሉት ካርቶኖች ለማጓጓዝ እንዲመች በአንድ እየታሸጉ ወደ ማቀዝቀዣ ክፍል ይገባሉ። በዚያም የሚኖረው ቆይታ ሳይበላሽ ወደ ታሰበለት ቦታ እስከሚደርስ ይሆናል። ለዓለምአቀፍ ገበያ የሚቀርቡት የአቮካዶ ምርቶች በዚህ መልኩ በጥንቃቄ እና በክትትል የተዘጋጁ ናቸው።
ይህን አይቶ ትኩስ (fresh) የኢትዮጵያ አቮካዶዎችን የማይገዛስ ማነው?
Facebook
Twitter
LinkedIn