ከኢትዮጵያ መነሻውን ያደረገው በአማራ ክልል በ200 ሄክታር መሬት ላይ የተመረተ 1600 ኩንታል የአቮካዶ ምርት፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ከሚሰራባቸው ወረዳዎች አንዱ ከሆነው ምዕራብ ጎጃም ዞን ፣ሰሜን ሜጫ ወረዳ ተነስቶ የውጪ ገበያውን ተቀላቅሏል።
በወረዳው አቮካዶ ከሚያመርቱ 447 አርሶ አርሶአደሮች ውስጥ ልፋታቸው ፍሬ አፍርቶ ምርቱ ደርሶላቸው ወደ ውጪ የላኩት 156 አርሶአደሮች ናቸው፡፡ ከእነዚህ አርሶአደሮች ተሰብስቦና ተገቢውን ምዘና አልፎ በጥንቃቄ የታሸገው የአቮካዶ ምርት ከኢትዮጵያ መሆኑን በሚገልፅ ማሸጊያ ተደርድሮ ወደ ባህርማዶ ገበያ ተጉዟል።
Facebook
Twitter
LinkedIn