በአማራ ክልል በመጪው ታህሳስ ወር መጀመሪያ ከሚሰበሰበው የበቆሎ ምርት 15.8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል፤
በ25 ወረዳዎች፣ በ541 ቀበሌዎች፣ በ3,332 ክላስተሮች በተደራጁ 570,995 አርሶ አደሮች የለማው የበቆሎ እርሻ 263,380 ሄክታር መሬት ይሸፍናል፡፡ ይህም ምርት በሚሰበሰብበት ወቅት ሰፊ የአገር ውስጥ ገበያ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡
በቆሎ በግ.ት.ኤ. የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮጀክት ድጋፍ ከሚመረቱ ሰብሎች አንዱ ሲሆን የበቆሎ አምራች አርሶ አደሮች በክላስተር የተደራጁ፣ ስለ በቆሎ የአመራረት ፓኬጅ ስልጠና የወሰዱና በግብርና ቢሮና በግ.ት.ኤ. ባለሙያዎች ክትትልና ድጋፍ የተደረገላቸው ናቸው፤ በክላስተሩ 71,725 ሴት አርሶ አደሮች ይገኛሉ፡፡
Facebook
Twitter
LinkedIn